ዲቮሽን
ቁ.120/07 ሐሙስ፣ ታህሳስ 30/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
ሩጫዎትን ሲሮጡ!
.…እኛ ደግሞ ቶሎ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከብበንን ሃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ (ዕብ 12፡ 1-2)፡፡
የእምነት ሩጫ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው መስመር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው! የእምነታችን ራስና ፈጻሚው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!
ታውቃላችሁ፥ የእምነት ሩጫ ያለ ዓላማ አይሮጡም! የእምነት ሩጫ የሚሮጠው የእምነታችንን ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክቶ እንጂ፥ የራስ መስመር ሰርቶ የራስ መንገድ አበጅቶ አይደለም!
ወገኖች ሆይ፥ የእምነት ሩጫው እንዳይደናቀፍ፥ ሩጫችንን ስንሮጥ ሁለት ነገሮች እናስወግድ--(1ኛ) ሽክምን፥ (2ኛ) ሀጢአትን!
ወገኖች ሆይ፥ ሩጫ እና ሸክም አብረው አይሄዱም! ስለሆነም፥ የኑሮ ሸክምን፥ የእህል ውሃ ሽክምን፥ ማናቸውንም ሸክምን ከራሳችን ላይ ልናራግፍ ይገባል!
ወገኖች ሆይ፥ የሚያስጨንቀንን፥ እረፍት የነሳንን፥ አቅም ያሳጣንን ማናቸውንም ሸክም ከራሳችን አውርደን፥ኒ ከትከሻችን ጥለን ሩጫችንን በነጻነት ልንሮጥ ይገባል!
ወገኖች ሆይ፥ የእምነት ሩጫ ሲሮጡ በሀጢአት ተከብቦ መሮጥ አይቻልም! ስለሆነም፥ የድፍረት ሀጢአታችንን፥ የስሀተት ሀጢአታችንን፥ አውቀን የምንሰራውን፥ ሳናውቅ የምናጠፋውን ማናቸውንም ሃጢአት ተናዝዘን ልንሮጥ ይገባል!
ወገኖች ሆይ፥ የክርስቶስ ኢየሱስ ደም የማያነጻው ሀጢአት የለምና፥ የእምነት ሩጫ ስንሮጥ፥ ሀጢአታችንን በደሙ ታጥበን ልንሮጥ ይገባል!
ወገኖች ሆይ፥ ከሩጫ ሜዳ ሲገቡ፥ የተሰመረውን መስመር እየተመለከቱ ይሮጣሉ እንጂ፥ ወዲያና ወዲህ እየተቅበዘበዙ፥ ወደኋላ ወደጎን እየተመለከቱ አይሮጡም!
ወዳጄ ሆይ፥ የእምነት ሩጫዎትን እንዴት እየሮጡ ነው? የእምነትዎን ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እየተመከቱ? ወይስ፥ ከመንገዱ ውጭ፥ ከመስመሩ ውጭ እየተወላገዱ?
-----
ትምህርቱ ጠቅሞታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!
--------------------------------
‹‹የወንጌላዊ እጮኛ›› በሙሉጊዜ አገልጋዮች ላይ የሚያጋጥሙ እውነተኛ ታሪኮች
የያዘ በሺዎች የተደነቀ ልብ አንጠልጣይ መጽሐፍ፣ በገበያ ላይ ውሏል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በ0911 678158 ወይም 0911
813092 ይደውሉ፡፡
No comments:
Post a Comment