ዲቮሽን
ቁ.142/07 አርብ፣ ጥር 22/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
ተስፋ አትቁረጥ!
እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥
የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው (ዕብ
11፡1)።
የሰው ልጆች ሁሉ ሥጋዊና መንፈሳዊ የሆኑ ውስጣዊና ውጫዊ ፍላጎቶች አሉን፡፡
እነዚህን ሥጋዊና መንፈሳዊ የሆኑ ውስጣዊና ውጫዊ ፍላጎቶች ለማሟላት፣ በሥራና በትምህርት እንዲሁም በልዩ ልዩ መንገዶች ለማሳካት
ጥረት እናደርጋለን፡፡ አንዳንዴ እነዚህ ጥረቶቻችን እንደተመኘነው ሲሳኩልን፣ አንዳንዴም ሳይሳኩልን ይቀራሉ፡፡ እነዚህ ሥጋዊና መንፈሳዊ
የሆኑ ውስጣዊና ውጫዊ ፍላጎቶች ‹‹ተስፋ›› ይባላሉ!
ታውቃላችሁ፣ ተስፋ የሕይወት ጣዕም ነው!
ይህ ጣዕም ሲጠፋ ሕይወት ውሃ ውሃ ማለት ይጀምራል! ሕይወት ውሃ ውሃ ሲል
ደግሞ መኖር ትርጉም ያጣል፡፡ መኖር ትርጉም ሲያጣ አለመኖር ይከተላል!
ወገኖች ሆይ፣ አማኞች ሥጋዊና
መንፈሳዊ የሆኑ ውስጣዊና ውጫዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሳካት፣ በሥራና
በትምህርት ላይ ብቻ አይተማመኑም! የአማኞች ተስፋ ካስማው የተተከለው፣ የሕይወታቸው
መልሂቅ በጥብቅ የታሰረው፣ ድርና ማጋቸው የተቆላለፈው፣ ዕጣና ፈንታቸው የተመሠረተው – በእምነት ላይ ነው!
ወገኖች ሆይ፣ እምነት
ምንድነው! እምነትም ማለት ገና ያላየነውን ነገር፣ ‹‹ይሆናል›› ብለን ተስፋ የምናደርግበትና ተስፋ
ያደረግነውም ነገር እንደሚፈጸም የምንረዳበት ማረጋገጫ ነው! የእምነታችን ዋስትና
እግዚአብሔር ራሱ ነው!
ታውቃላችሁ፣ እምነት ለተስፋችን መፈጸም ማረጋገጫ ነው!
የመጽሐፍ ቅዱስ አባቶች የተመሰከረላቸው በዚሁ መንገድ ነው!
ወገኖች ሆይ፣ ተስፋ መቁረጥ የሕይወት ጸር ነው፣ ተስፋ
መቁረጥ የሕይወት አደጋ ነው! ተስፋ መቁረጥ ሲኖር ብርሃን ይጨልማል፣ ተስፋ መቁረጥ ካለ
ተራ ነገር እንኳ ውስብስብ ይሆናል! ስለሆነም ተስፋ መቁረጥ ይቅር!
-----
ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!
ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!
--------------------------------
‹‹የወንጌላዊው እጮኛ›› አዲስ መጽሐፍ፣ በገበያ ላይ ውሏል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ
በ0911 678158 ወይም 0911 813092 ይደውሉ፡፡
No comments:
Post a Comment