ዲቮሽን
ቁ.138/07 ሰኞ፣ ጥር 18/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
ለእኛ የሚያስበው !
ለእናንተ የማስባትን
አሳብ እኔ አውቃለሁ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም (ኤር 29፡11)።
ይህ መልዕክት
በምርኮ ምድር በባቢሎን ለነበሩ አይሁዳዊያን የተነገረ ነው፡፡ በበደላቸውና በኃጢአታቸው ምክንያት ከምድራቸው ተነቅለው፣ በምርኮ
ሀገር በባዕድ መሬት ለሚኖሩ የእግዚአብሔር ሰዎች የተነገረ መልዕክት!
ወገኖች ሆይ፣
ይህ መልዕክት በቅጣት ላይ ለሚገኝ የእግዚአብሔር ሕዝብ የተነገረ መልዕክት ነው! ሕዝቡ በቅጣት ላይ ቢገኝም፣ በምርኮ ላይ ቢገኝም፣
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል – ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ! … መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ!
ወገኖች ሆይ፣
የእግዚአብሔር ሕዝብ በበደላቸውና በኃጢአታቸው ምክንያት ከቦታቸው ተነቅለው፣ በቅጣት በትር ሥር፣ በምርኮ ሀገር ቢገኝም፣ እግዚአብሔር
እንዲህ ይላል– ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ! ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር
አይደለም!
ታውቃላችሁ፣ በበደላችንና
በኃጢአታችን ምክንያት እግዚአብሔር ቢቆጣም፣ በሠራነው ክፋት ጌታ ቢቀጣንም፣ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ
የክፉ ነገር አይደለም! ለእኛ ያለው ሐሳብ፣ ፍጻሜና ተስፋ የተሞላ የሰላም አሳብ እንጂ የክፉ አይደለም!
ታውቃላችሁ፣ በበደላችንና
በኃጢአታችን ምክንያት እግዚአብሔር ቢቆጣም፣ በሠራነው ክፉ ቢቆነጥጠንም፣ ለእኛ ያለው እቅድ፣ ፍጻሜው ያማረ፣ ለእኛ የሚጠቅም፣
ተስፋ የሚሰጥ እንጂ፣ የሚጎዳ አይደለም! ሐሳብ፣ ፍጻሜና ተስፋ የተሞላ የሰላም አሳብ እንጂ የክፉ አይደለም!
ታውቃላችሁ፣ ጌታ
ሲገስጸን ሰርቶ አስተካክሎ፣ ጊዜውን ጠብቆ ይጎበኛል እንጂ ጥሎ አይተወንም! የቅጣት ጊዜያችን፣ የእንባ
ቆይታችን በተፈጸመ ጊዜ በስሙ ስንጸልይ፣ ስሙን ስንጠራ ይሰማናል እንጂ ችላ አይለንም!
የቅጣት ጊዜያችን፣ የእንባ ዘመናችን በተፈጸመ ጊዜ በፍጹም ልባችን አጥብቀን ብንሻው ይገኝልናል እንጂ ፊቱን አይሰውርም!
No comments:
Post a Comment