ዲቮሽን
ቁ.137/07 እሁድ፣ ጥር 17/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
‹‹ና››
በለኝና !
ጴጥሮስም መልሶ፦
ጌታ ሆይ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ አለው። እርሱም፦ ና አለው። ጴጥሮስም ከታንኳይቱ ወርዶ ወደ
ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ (ማቴ 14፡28-29)።
ጌታዬ ሆይ፣ የወግ
የልማድ መመላለስ በጣም ሰልችቶኛል! የተአምራት ጉዞ፣ በተአምራት መመላለስ እጅጉን አምሮኛል! ተአምራት እርቦኛል፣ ተአምራት ጠምቶኛል!
ጌትዬ፣ በውሃ ላይ መሄድ አምሮኛል! እባክህ ጌታዬ ጴጥሮስን እንዳልከው፣ እኔንም
‹‹ና›› በለኝና በተአምራት ልራመድ፣ በተአምራት ልሂድ! በተአምራት ልውጣ፣ በተአምራት ልግባ! በተአምራት ልሥራ በተአምራት ልብላ!
ጌትዬ፣ በንፋሱ
መሀል፣ በማዕበሉ መሀል፣ ‹‹ና›› በለኝና በተአምራት ልውጣ! አቢዬ፣ ‹‹ና›› በለኝና ከስጋቴ – ከፍርሃቴ ልውጣ!
አምላክዬ፣ ‹‹ና›› በለኝና ከጭንቀቴ – ከተግዳሮቴ ልውጣ፣ አባቢዬ፣ ‹‹ና›› በለኝና ከእስራቴ – ከሕማማቴ ልውጣ! አባቴ፣
‹‹ና›› በለኝና ከውድቀቴ – ከውርደቴ ልውጣ! ረዳትዬ ‹‹ና›› በለኝና ከሽንፈቴ – ከስብራቴ ልውጣ! የማመልክህ ጌታ ‹‹ና››
በለኝና ከወግ ከልማዴ ልውጣ!
No comments:
Post a Comment