ዲቮሽን
ቁ.131/07 ሰኞ፣ ጥር 11/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
ያልተጠመቀው – ጥምቀት !
በጥምቀትም ከእርሱ ጋር
ተቀብራችሁ፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ፥ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ። (ቆላ 2፡12)፡፡
እውነተኛ አማኝ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኙ አድርጎ በተቀበለ ቅጽበት ዳግመኛ
ይወለዳል፡፡ ይህ ዳግመኛ ልደት አዳማዊ እና አሮጌውን ማንነት በመግፈፍ እና በማስወገድ አዲስ ሕይወት ልምምድን ይተካል፡፡
ዳግመኛ ልደት የሥጋን
ሰውነት በመግፈፍ፥ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በክርስቶስ መገረዝን ያመጣል፡፡ የዚህ መንፈሳዊ አሠራር ምሳሌ የሚሆነው የውሃ ጥምቀት
ነው! ጥምቀት ከክርስቶስ ጋር ተቀብረን፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችን፥ ከክርስቶስ ጋር
መነሣታችንን ያሳያል!
ወገኖች ሆይ፣
ዓመት ጠብቀን የምናከረው የ‹‹ጥምቀት›› በዓል፣ ዳግመኛ የመወለዳችንን ምሳሌ እየሆነ ነውን? በ‹‹ጥምቀት›› በዓላችን ሲደረጉ የምናስተውላቸው ሁነቶች በእውነቱ
በክርስቶስ አምነን መዳናችንን የሚመሰክሩ ድርጊቶች ናቸውን?
ወገኖች ሆይ፣
ወቅት እየጠበቅን በልዩ ድምቀት የምናከረው የ‹‹ጥምቀት›› በዓል፣ በበዓላችንም ጊዜ ሲከናወኑ የምናያቸው ነገሮች መንፈሳዊ ለውጥ ማግኘታችንን፣
የሥጋን ሰውነት በመግፈፍ፥ በእጅ ባልተደረገ
መገረዝ በክርስቶስ የመገረዛችንን እውነታ እያሳዩን ነውን?
ወገኖች ሆይ፣
ቅዱስ ቃሉ እንደሚል፣ ጥምቀት ከክርስቶስ ጋር ተቀብረን፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችን፥
ከክርስቶስ ጋር መነሣታችንን ያሳያል! ነገር ግን በየዓመቱ በምናከብረው ‹‹ጥምቀት›› ሲደረጉ የምናቸው ዓለማዊ ድርጊቶች ከክርስቶስ
ጋር የመቀበራችንን እውነታ ያመለክታሉን?
ታውቃላችሁ፣ ‹‹ለጥምቀት
ያልሆነ ልብስ ይበጣጠስ›› ነውና፣ ሕዝባችን ተበድሮም ሆነ ተለቅቶ በዓሉን በአዲስ ልብስ ያከብራል! የጥምቀት በዓላችን በአልባሳት
ኅብረ ቀለማት ባሸበረቀ ሁኔታ በየጥምቀተ ባህሮችና የሕዝብ አደባባዮች ደምቆ ይከበራል፡፡ ይህም ድምቀት ዓለማቀፋዊ ዝናን ስላጎናጸፈለት
በዓላችን በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል!
ታውቃላችሁ፣ ጥምቀታችን
ዓለማዊ ዝናን ተጎናጽፎ በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ እንጂ፣ መንፈሳዊ ዝና ተጎናጽፎ ልናየው አልቻልንም! በጥምቀት በዓላችን ሲደረጉ
የምናያቸው ከጽድቅ የተጣሉ ዓለማዊ ድርጊቶች እንጂ፣ የጽድቅ ምሳሌዎች ሊሆኑ አይችሉም!
ታውቃላችሁ፣ በበዓላችንም
ጊዜ ሲከናወኑ የምናየው ዳንሱና ዳንኪራው፣ አስረሽ ምችው ጭፈራው፣ ቁማሩ ስካሩ፣ ጫቱና ዝሙቱ ፣ ሲጋራና ሺሻው፣ የቡድን ጸቡና ስድድቡ፣ ሌሎችም በርካታ ነገሮች
መንፈሳዊ ለውጥ ማግኘታችንን፣ የሥጋን
ሰውነት በመግፈፍ፥ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በክርስቶስ የመገረዛችንን እውነታ የሚያሳዩ አይደሉም!
ታውቃላችሁ፣ በበዓላችንም
ጊዜ ሲከናወኑ የምናያቸው ነገሮች ዳግመኛ አለመወለዳችንን፣ የጽድቅ ስራ ለመስራት አቅም ማጣታችንን፣ መንፈሳዊ ለውጥ አለማግኘታችንን፣
የሥጋን ሰውነት መግፈፍ አለመቻላችንን፥
በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በክርስቶስ ያለመገረዛችንን እውነታ ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ ናቸው!
ወገኖች ሆይ፣
ጥምቀታችን ለራሱ ገና አልተጠመቀም! ተጠማቂዎቹም ገና የሥጋን ሰውነት መግፈፍ ባለመቻላችን ከክርስቶስ ጋር አልተቀበርንም! ከክርስቶስ
ጋር ካልተቀበርን ደግሞ፣ የሙታን ትንሳኤ ልናገኝ አንችልም!
-----
ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!
ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!
--------------------------------
‹‹የወንጌላዊ እጮኛ›› አዲስ መጽሐፍ፣ በገበያ ላይ ውሏል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ
በ0911 678158 ወይም 0911 813092 ይደውሉ፡፡
No comments:
Post a Comment