ዲቮሽን
ቁ.116/07 እሁድ፣ ታህሳስ 26/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
የሰላም ማሰሪያ!
በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ (ኤፈ 4፡3)።
መንግሥታት ለሰላም እጅግ ከፍ ያለ ዋጋ ያወጣሉ፡፡ ምክንያቱም
ለሀገር ልማትና ዕድገት ሰላም አይነተኛ ሚና ስለሚጫወት ነው፡፡ በርግጥ፣ ሰላም በሌለበት ምንም አይነት የተረጋጋ ውሳኔ ማድረግ
አይቻልም፡፡ ሰላም በሌለበት የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ እቅድ መያዝም አይታሰብም፡፡ ስለሆነም፣ መንግሥታት ለሰላም የሚሰጡት
ቦታ፣ ለሰላም የሚከፍሉት ዋጋ፣ ለሰላም የሚዘምሩት ዜማ ሊደነቅ ይገባል፡፡
መንግሥታት ለሰላም የሚያቆሙት ዘብ፣ ለሰላም የሚሠሩት ግንብ፣
የሚደረድሩት አጥር፣ የሚደግድጉት ቅጥር ሊደነቅ ይገባል፡፡ ሆኖም፣ ቃሉ እንደሚል፣ ‹‹እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣ ጠባቂ በከንቱ
ይተጋል›› (መዝ 127፡1)፡፡ ስለሆነም፣ መንግሥታት ለሚያደርጉት የጥበቃ ትጋት ብናደንቃቸውም፣ ዋናው ጠባቂያችንና የሰላማችን
ምንጭ የሆነው እግዚአብሔር መሆኑን እናምናለን፣ እንመሰክራለንም!
ወገኖች ሆይ፣ ሰላም ለሰው ልጆች ሁሉ እጅግ ወሳኝ ነገር ነው፡፡
ሰላም በቤት ውስጥም ሆነ ውጭ፣ በሥራ ቦታም ሆነ በማናቸውም ሥፍራ እጅግ ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ሰላም የሌለበት አንድነት አንድነት
የሌለበት ምንም ነገር የለም፡፡ ምንም የሌለበት ሕይወት አይገኝም፡፡ ሕይወት የሌለበት መኖር ደግሞ የለም፡፡
ወገኖች ሆይ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ
የሰላም ማሰሪያ ሊኖር ግድ ይላል! የሰላም ማሰሪያው ደግሞ ፍቅር ነው፡፡ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን
አንድነት ለመጠበቅ መትጋት ሲያስፈልግ፣ ለሰላም ማሰሪያው ደግሞ ፍቅርን ለመጠበቅ መትጋት ያስፈልጋል፡፡
--------
ትምህርቱ ጠቅሞዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፡፡ ጌታ
ይባርክዎ!
--------------------------------
‹‹የወንጌላዊ እጮኛ›› በሺዎች የተደነቀ ልብ አንጠልጣይ መጽሐፍ፣ ፒያሳ ከሚገኘው
በእምነት መጻሕፍት መደብር ፒያሳ፣ በራዕይ መጻሕፍት መደብሮች፣ መካነየሱስ መጻሕፍት መደብር፣ የምሥራች ድምጽ መጻሕፍት
መደብሮች፣ መሠረተክርስቶስ መዝሙር ቤት ስቴዲዮም ያገኛሉ፡፡ የመጽሐፉ ዋጋ 40 ብር ነው፡፡ በአዲስ አበባ የምትገኙ ወገኖች
መጽሐፉ ያሉበት ድረስ እንዲመጣላችሁ ከፈለጋችሁ፣ በ0911 678158 ወይም 0911 813092 ይደውሉ፣ በሰዓታት ውስጥ
ይመጣላችኋል፣ ነገር ግን ለትራንስፖርት 10 ብር ጭማሪ ይከፍላሉ፡፡
No comments:
Post a Comment