ዲቮሽን
ቁ.108/07 ቅዳሜ፣ ታህሳስ 18/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
ሰብዓ
ሰገል!
ኢየሱስ በቤቴልሔም ከተማ ተወለደ፡፡ የክዋክብት ተመራማሪዎች
የምሥራቅ አገር ሰዎች ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው፣ በቅርቡ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ የሚገኘው የት ነው?
በምሥራቅ አገር ሆነን ኮከቡን ስላየን ልንሰግድለት መጥተናል (ማቴ 2፡1-2)።
ጠቢባኖቹ ከምሥራቅ አገር፣ ራቅ ካለ አካባቢ የመጡ ናቸው፡፡
ምናልባትም ከሜዶ-ፐርዥያ ግዛት አካባቢ የመጡ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ እነዚህ ጠቢባን ስለ መሲሁ መወለድ በሜዶንና ፋርስ ግዛቶች ከተበታተኑ የእስራኤል ዲያስፖራዎች፣ በተለይም ከቤተመንግሥቱ ቁልፍ
ባለሞያሞች ቁንጮ ከሆነው ከነቢዩ ዳንኤል (ዳን 9) ሳይሰሙ አልቀሩም፡፡
ወገኖች ሆይ፣ እዚህ ባዕዳን የኮከብ ተመራማሪዎች የነቢዩን ዳንኤል
ትንቢት መርምረውና የአይሁዱን ንጉሥ የልደት ጊዜ አስልተው ሊሰግዱለት ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡
ታውቃላችሁ፣ እስራኤላዊያን
ያልሆኑ ኮከብ ተመራማሪዎች አዲስ ለተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ሊሰግዱለት
ከምሥራቅ
ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጡ፣ በኢየሩሳሌም የነበሩ የሥነመለኮቱ ሊቆች፣ ፈሪሳዊያን፣ ሰዱቃዊያን፣ መምህራን፣ ካህናት፣ የሕዝብ አለቆችና
ባለሥልጣናት የኢየሱስ ክርስቶስን መወለድ አላወቁም፡፡
ታውቃላችሁ፣ ለድንግሊቱ
ማርያም መልዐኩ ገብርዔል የነገራትን መልዕክት፣ የኤልሳቤጥ ጽንስ ለማርያም ጽንስ የዘለለበትን ሚስጥር፣ በእረኞቹ ዙሪያ መላዕክት
ተገልጠው ያቀረቡትን መዝሙር፣ የኢየሩሳሌም የሐይማኖት መሪዎች መረጃ የላቸውም፡፡
ታውቃላችሁ፣ ሐይማኖተኝነታችን
ጌታን አያሳየንም፡፡ የኛ ሊቃውንትነት፣ የኛ ሕግ አዋቂነት፣ መጻሕፍት አዋቂነት፣ ሐይማኖተኝት፣ የሕዝብ መሪነት፣ መምህርት፣ ጌታን
አያሳይም፡፡ እነዚህ ሁሉ በኢየሩሳሌም የነበሩ የሥነመለኮት ሰዎች መወለዱን ሳያውቁ፣ ከሩቅ አካባቢ የመጡ ኮከብ ተመራማሪዎች መወለዱን
አወቁ፡፡
ታውቃላችሁ፣ ወግና
ልማዳችን ጌታን አያሳየንም፡፡ የሐይማኖት ተቆርቋሪነታችን ጌታን አያሳየንም፡፡
ወገኖች ሆይ፣ ጌታን
የምናየው በእውነተኛ ልብ ስንፈልገው ነው፡፡ ዋና ዓላማችን ራስን በማዋረድ ጌታን ማምለክ ሲሆን፣ ጌታን እናያለን፡፡ ከከፍታ ወርደን፣
ራሳችንን ክደን እርሱን ማመን ስንችል፣ ጌታን እናያለን፡፡ ሌላ ነገር ትተን፣ የተገለጠልንን ሕይወት፣ የበራልንን እውነት ተከትለን
ስንሄድ ጌታን እናያለን፡፡
--------------------------------
‹‹የወንጌላዊ
እጮኛ›› በሺዎች የተደነቀ ልብ አንጠልጣይ መጽሐፍ ነገ፣ እሁድ፣ ታህሳስ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡00 ይመረቃል፡፡
ካዛንቺስ ኡራኤል መካነየሱስ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት እንዲገኙልኝና ይህንን
ታሪካዊ መጽሐፍ እንዲመርቁልኝ በአክብሮት ጋብዤዎታለሁ፡፡
No comments:
Post a Comment