ዲቮሽን ቁ.95/07 እሁድ፣ ታህሳስ 5/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
የጠራቸውን የሚያውቁ መሪዎች !
የእግዚአብሔርም መልአክ (ለጌዴዎን) ተገልጦ። አንተ ጽኑዕ ኃያል ሰው፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው አለው።…እግዚአብሔርም ወደ እርሱ ዘወር ብሎ። በዚህ በጕልበትህ ሂድ፥ እስራኤልንም ከምድያም እጅ አድን እነሆ፥ ልኬሃለሁ አለው (መሳ 6፡12-13)፡፡
አንድ መሪ ወደ አመራር አገልግሎት ከመምጣቱ በፊት፣ ለመሪነት የጠራውን ጌታ ማንነት ሊረዳ ይገባል፡፡ ይህም ለአገልግሎቱ በረከትን ያስገኝለታል፡፡ ጌዴዎን የአመራር ጥሪ ተቀብሎ በመሪነት አገልግሎት ከመሠማራቱ በፊት የጠሪውን ማንነትና ብቃት በሚገባ ፈትሾና አረጋግጦ ነው የገባበት፡፡ የበግ ጠጉር ባዘቶ በአውድማ ላይ አስቀምጦ፣ እግዚአብሔር ለአመራር ጠርቶት ከሆነ ምድሩ ሁሉ ደረቅ ሆኖ ባዘቶው ላይ ብቻ ጤዛ እንዲኖር ጠየቀ፡፡ ጌታ ይህንን ምልክት ሲያደርግ፣ ተቃራኒውን ደግሞ ጠየቀ፡፡ ምድሩ ሁሉ ጤዛ ሆኖ፣ ባዘቶው ላይ ብቻ ደረቅ እንዲሆን፡፡ ጌታ ይህንንም እንደጠየቀው አደረገለት፡፡
ወገኖች ሆይ፣ የጌዴዎን ፍተሻ ከባድ መሆኑን ከክፍሉ ማየት እንችላለን! ጌዴዎን፣ ለእግዚአብሔር ያቀረበለት መስቀለኛ ጥያቄዎች፣ የጠሪውን ማንነት በትክክል ለማረጋገጥ ነበር!
ወገኖች ሆይ፣ ጌዴዎን በጥያቄ ብቻም ሳይወሰን፣ በተግባር ሊዳሰሱና ሊጨበጡ የሚችሉ ምልክቶችን ይጠይቅ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን እንድንመራ በእውነትም ጠርቶን ከሆነ፣ ምልክቶች ይሰጠናል(መሳ 6፡36-37)፡፡
ወገኖች ሆይ፣ እግዚአብሔርን የእኛ የምልክት፣ ድንቅና ተአምራት ጥያቄ አያሳስበውም፡፡ ሁሉ በእጁ፣ ሁሉ በደጁ ነው፡፡ መጠራታችንን እርግጠኛ ሳንሆን በማይሆን የአመራር ቦታ ከምንቀመጥ፣ ለእርግጠኝነቱ ከእግዚአብሔር ምልክቶችን መጠየቁ ስህተት አይሆንም፡፡ ስህተቱ፣ ጠሪውን አለማወቅ፣ ጥሪን ሳያረጋግጡ ወደ አመራር መሮጥ ነው!
--------------------------------
(ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክና ሼር ያድርጉ፣ ወዳጅ ጓደኞችም እንዲያገኙ ያግዙ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!)

No comments:
Post a Comment