ዲቮሽን ቁ.84/07
ረቡዕ፣ ሕዳር 24/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን
ሐጢያ)
የጴንጠቆስጤነት አቡጊዳ(#4) –ነቀፋ፣ ሹፈትና ውግዘት!
ሁሉም
ተገረሙና አመንትተው እርስ በርሳቸው። እንጃ ይህ ምን ይሆን? አሉ። ሌሎች ግን እያፌዙባቸው። ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል አሉ(የሐዋ 2፡12-13)፡፡
ወገኖች
ሆይ፣ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ባለበት ቦታ ሁሉ፣ ባንድ ወገን አግራሞትና አድናቆት፣ በሌላ ወገን ደግሞ ነቀፋና ሹፈት አይጠፋም!
እውነተኛ የጴንጠቆስጤ እንቅስቃሴ ሲኖር ከእንቅስቃሴው ጋር አብሮ አነጋጋሪ ነገር መኖሩ ያለ፣ የነበረና ለወደፊትም የሚኖር እውነታ
ነው!
ወገኖች
ሆይ፣ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በመጽሐፍ ቅዱስ በምናውቃቸው ክስተቶች ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ የመንፈስ ቅዱስን መለኮትነት
የምናምን ከሆነ፣ የእግዚአብሔር ማንነትና ሥራ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰልን ብቻ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ማንነት በመጽሐፍ
ቅዱስ ከተጠቀሰልን በተጨማሪ ሌሎችም ብዙ የማናውቃቸው እውነታዎች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ከመታወቅ ያልፋልና፣ በመጽሐፍ
ቅዱስ ገጾች አይወሰንም፡፡
ይህን ነጥብ ለመረዳት፣ ዶናልድ ሲ. ስታምፕስ፣ በምሉዕ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ
መግቢያ ላይ ያሰፈረውን ሐሳብ ቆም ብለን ብናሰላስል ይጠቅመናል፡፡ እንዲህ ይላል፣ ‹‹መንፈስ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች አይወሰንም፣
ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን እንደሠራ ሁሉ ዛሬም መሥራት ይፈልጋል›› ምሉዕ ሕይወት አማርኛው ትርጉም፣ 2010 Life Publishers International.
ወገኖች
ሆይ፣ ከላይ የተጠቀሰው ሐሳብ ግራ እንዳያጋባን እስኪ ጥቂት ማብራሪያ ልስጥ፡፡ የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ያለባቸውን ቦታዎችና
የተቀቡ አገልጋዮችን አስቡ፡፡ በእነዚህ ቦታዎች የሚደረጉ ድንቆችና ተአምራቶችም አስቡ፡፡ አንዳንድ ሁነቶች በመጽሐፍ ቅዱስ
ከተጠቀሱ ታሪኮች ጋር ይመሳሰላሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ፈጽሞ አይመሳሰሉም፡፡ የሚመሳሰሉት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች ስላሏቸው
አነጋጋሪ አይሆኑም፡፡
ወገኖች
ሆይ፣ አነጋጋሪ የሚሆኑት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ ተደርገው ያልተጠቀሱ ክስተቶች ናቸው፡፡ እነዚህን ክስተቶች
አንዳንዶች ስለማይዋጥላቸው አይቀበሉም፡፡ አንዳንዶቹ አለመቀበል ብቻም ሳይሆን አገልጋዮቹንና አገልግሎቶቹን ሲነቅፉና ሲያሾፉ
ይታያል፡፡ ሌሎቹም፣ አገልጋዮቹንና አገልግሎቶቹን ከእውነት የሳቱ፣ አጋንንታዊ አድርገው ይቆጥሯቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ በዚህ ብቻም
አያበቁም! ጉባኤ ሰብስበው መግለጫ ሲያወጡ እና ሲያወግዙም ይታያል፡፡
ወገኖች
ሆይ፣ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በመጽሐፍ ቅዱስ በምናውቃቸው ክስተቶች ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፈው
ከምናውቃቸው ክስተቶች ውጭም (Extra Biblical Manifestations) መንፈስ ቅዱስ ሊሠራ ይችላል፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን
ይችላል?
ወገኖች
ሆይ፣ ይህ ሊሆ የሚችለው፣ መንፈስ ቅዱስ በእውነተኛ ክርስቲያኖችና አገልጋዮች ላይ ሲወርድ ነው!
መንፈስ ቅዱስ በእኛ ላይ ሲወርድ ኃይልን እንቀበላለን! የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ስንቀበል በመካከላችን ድንቆችና
ተአምራቶች ሊደረጉ ይጀምራሉ፡፡ በየሳምንቱ፣ በየወሩ፣ በየአዓመቱ ስብሰባ እየተደረገ፣ ነገር ግን ከሳምንታት እስከ ከወራት፣
ከወራት እስከ ዓመታት ድንቆችና ተአምራቶች የማይደረግባቸው ቦታዎች፣ ኃይል አልባ ናቸው ብሎ ማሰብ፣ መደምደምም ይቻላል!
ወገኖች
ሆይ፣ ጴንጠቆስጤነትና የኃይል አገልግሎት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው! ጴንጠቆስጤነትና የኃይል
አገልግሎት የተጣመሩ ቢሆኑም ሥራ ለመጀመር ግን የሚያምኑ ሰዎችን መኖር ይጠይቃሉ፡፡ እምነት የሌለበት ቦታ የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ
በኃይል አይገለጥም፡፡ እምነት የሌለበት ድንቆችና ተአምራቶች ሊታዩ አይችሉም፡፡
ከሰው
ፍልስፍና ይልቅ፣ እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያደረጉ፣ የተስፋውን ቃል ለመቀበል በእምነት የሚጸልዩ፣ በመንፈስ ቅዱስ
ይጠመቃሉ፣ በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቁ ኃይልን ይቀበላሉ፡፡ ኃይል ሲቀበሉ ከኢየሩሳሌም ጀምሮ፣ በይሁዳና ሰማርያ እስከ ምድር ዳርም ድረስ የክርስቶስ ምስክሮች ይሆናሉ።
ወገኖች
ሆይ፣ በነቢያትና ሐዋሪያት በሚጠቀሟቸው የዘይት፣ የውሃ፣ የጨርቅ፣ ወይንም ሌሎች ያልተለመዱ ቁሳቁሳዊ አገልግሎቶች ነገሮች ላይ
ብዙ ጊዜ አሉታዊ ነቀፋ ቢሰነዘርም፣ ሚዛን የጎደለው ውግዘት ቢደረግም፣ እነዚህ ነቀፋዎችና ውግዘቶች እውነትነት አላቸው ማለት አይቻልም፡፡
መንፈስ ቅዱስ በኃይል መሥራት ሲጀምር ያልተለመዱ ነገሮች መሆናቸው፣ ያልታወቁ ሚስጥሮች መገለጣቸው፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተመዘገቡ
አነጋጋሪ የሆኑ አገልግሎቶችና ልምምዶች መኖራቸው ያለ፣ የነበረና ለወደፊትም የሚኖር እውነታ ነው!
ወገኖች
ሆይ፣ ጴጥሮስ ወደቆርኔሌዎስ ቤት እንዲሄድ (የሐዋ 10) መንፈስ ቅዱስ ሲልከው ያደረገውን ክርክር አስቡ!
መንፈስ ቅዱስ ‹‹ተነሣና አርደህ ብላ›› ሲለው፣ ‹‹እርኩስ ነው፣ አጸያፊ ነው›› በማለት ተከራከረ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በድጋሚ፣
‹‹እግዚአብሔር ንጹህ ያደረገውን፣ አንተ እንደ እርኩስ አትቁጠረው›› በማለት ሞገተው፡፡
ወገኖች
ሆይ፣ መንፈስ ቅዱስ በኃይል መሥራት ሲጀምር ያልተለመዱ ነገሮች መሆናቸው አይቀሬ ነው!
እነዚህን ያልተለመዱ ነገሮች እግዚአብሔር ከተቀበላቸው፣ እኛ እንደንጹህ የማናቸውን እርሱ ንጹህ አድርጎ ከቆጠራቸው፣ እኛም
እንቀበላቸው፡፡ መቀበል ከቸገረን ግን ቢያንስ እንደ እርኩስ አንቁጠራቸው!
ወገኖች
ሆይ፣ በባህላችን ያልተለመዱ እንደ ኪቦርድ፣ ድራም፣ ጃዝ፣ ሳክሶፎን፣ ጊታር የመሳሰሉ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ቀስ በቀስ ለምደን
መጠቀም ጀምረናል፡፡ እነዚህን መሳሪያዎች ጌታ ለክብሩ አገልግሎት ቀድሶ ከተቀበላቸው እኛስ ምን አግዶን ነው ነቀፋና ትችት ውግዘት
የምናበዛው ?!
ወገኖች ሆይ፣ መንፈስ ቅዱስ በዘይት፣ በውሃ፣ በጨርቅ፣ ወይንም በማናቸውም ያልተለመዱ ሌሎች
ቁሳቁሶች ቢጠቀም፣ ክብሩን ቢገልጥበት፣ ሕዝቡን ቢያንጽበት፣ ፈውስን ቢያመጣበት፣ ድንቅና ተአምራት ቢፈጽምበት፣ እኛ ምን
አግዶን ነው ነቀፋ፣ ሹፈትና ውግዘት የምናበዛው ?!
--------------------------------
(ትምህርቱ
ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክና ሼር
ያድርጉ፣ ወዳጅ ጓደኞችም እንዲያገኙ ያግዙ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!)
No comments:
Post a Comment