ዲቮሽን ቁ.83/07
ማክሰኞ፣ ሕዳር 23/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን
ሐጢያ)
የጴንጠቆስጤነት አቡጊዳ(#3) – የሕዝብ መሰብሰብ!
ከሰማይም
በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፤ ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥
እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ።…ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ።…እኛም እያንዳንዳችን
የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን? (የሐዋ 2፡5-12)፡፡
ጴንጠቆስጤ
ሕዝብ ማራኪ ነው! መንፈስ ቅዱስ ሥራ ባለበት ቦታ ሁሉ፣ የጸጋ ስጦታ በሚሠራበት ቦታ ሁሉ ሕዝብ ይሰበሰባል፡፡ ጴንጠቆስጤነት
ብሔርና ቋንቋ፣ ጾታና ዜግነት ሳይለይ፣ ከቅርብም ከሩቅም፣ ከሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ሰዎችን ይማርካል፣ ይሰበስባል፡፡
ወገኖች
ሆይ፣ ስለማር ጠብታ አስቡ! የማር ጠብታ ያለበት ቦታ ንቦች ይሰበሰባሉ፡፡ ጴንጠቆስጤነት እንደ ማር ፈሳሽ ነው፡፡ የማር ፈሳሽ
ያለበት ቦታ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ንቦች እንደሚሰበሰቡ ሁሉ፣ መንፈስ ቅዱስ የሚሠራበትም ቦታ እንዲሁ ብዙ ሕዝብ ይሰበሰባል፡፡
ታውቃላችሁ፣
የማር ፈሳሽ በቤታችን ውስጥም ቢሆን ንቦች ያገኙትን ቀዳዳ ተጠቅመው ወደቤታችን ከመግባት አይመለሱም፡፡ በሩና መስኮቱ
ሲከፋፈትላቸው ቤታችን በንብ መንጋ ሊወረር ይችላል፡፡ ልክ እንደዚሁ፣ በመኖሪያ ቤታችንም ይሁን፣ በማናቸውም ስፍራ የጸጋ ስጦታ
የሚሠራበት ቦታ ሰዎች ይሰበሰባሉ፡፡
ታውቃላችሁ፣
መንፈስ ቅዱስ ሕዝብ ሰብሳቢ ብቻ አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ
የሕዝብን
ቋንቋ ያውቃል፡፡ ሕዝብ ቢበዛም፣ ብሔረሰብ ቢበዛም፣ ቋንቋ ቢበዛም፣ መንፈስ ቅዱስ ቋንቋ አዋቂ–የታወቀ ሊንጉይስት ነው!
ታውቃላችሁ፣
መንፈስ ቅዱስ የየራሳችንን ቋንቋ ይናገራል! የጸጋ ስጦታ የሚሠራበት ጉባኤ መንፈስ ቅዱስ በቋንቋችን ያነጋግረናል! ብዙ ሕዝብም
ብንሆን የእያንዳንዳችንን ቋንቋ፣ የእያንዳንዳችንን ጥያቄ፣ የእያንዳንዳችንን ጉዳይ፣ ያውቃል፡፡ በነፍሳችን ውስጥ፣ ከእርሱ
የተደበቀ ቋንቋ፣ ከእርሱ የተሰወረ ጨዋታ የለም!
ስለሆነም፣
የጸጋ ስጦታ በሚሠራበት ቦታ ሁሉ ሕዝብ ይሰበሰባል፣ የተሰበሰበው ሕዝብም በሚያየው ነገር ይገረማል፣ በሚሰማው ነገር ይደነቃል!
መንፈስ ቅዱስ አስገራሚ አምላክ፣ አስደናቂ ጌታ ነው! መንፈስ ቅዱስ ልባችንን የሚያይ፣ ስሜታችንን የሚረዳ፣ ቋንቋችንን
የሚያውቅ፣ ነፍሳችንን የሚያነብብ፣ አስደናቂ አምላክ ነው!
--------------------------------
(ትምህርቱ
ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክና ሼር
ያድርጉ፣ ወዳጅ ጓደኞችም እንዲያገኙ ያግዙ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!)
No comments:
Post a Comment