Sunday, December 7, 2014

የጴንጠቆስጤነት አቡጊዳ (#7) --የሐዋርያት ትምህርት

ዲቮሽን ቁ.87/07 ቅዳሜ፥ ሕዳር 27/07 ዓ/ም
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)

የጴንጠቆስጤነት አቡጊዳ (#7) --የሐዋርያት ትምህርት

በሐዋርያትም ትምህርትና በሕብረት፥ እንጀራውንም በመቁረስ በየጸሎትም ይተጉ ጀመር (የሐዋ 2፡42)

እውነተኛ ጴንጠቆስጤነት የሐዋርያትን ትምህርት እንደወረደ መቀበል እና መከተል ነው፡፡ ጴንጠቆስጤነት የሐዋርያትን እምነት፥ ኑሮና ልማድ እንደወረደ መቀበልና መከተል ነው፡፡

ታውቃላችሁ፥ ክርስቲያኖች በሙሉ ሐዋርያት ተብለው ይጠሩ ነበር፡፡ ታውቃላችሁ፥ ሐዋርያትነት የእውነተኛ ክርስትና እምነት ዋናው መፈተሻ ሚዛን ነው!

ታውቃላችሁ፥ ከሐዋርያት እምነትና ትምህርት የጎደለ ክርስትና ጤና የጎደለው ነው፡፡ "ቂም ይዞ ጸሎት" እንዲሉ፥ ሐዋርያዊነትን ጠልቶ ክርስትና፥ ከሐዋርያዊነት ወጥቶ ክርስትና የለም!

ታውቃላችሁ፥ ሐዋርያዊነት የክርስትናችን መገለጫ፥ የእምነታችን ማረጋገጫ ነው! ክርስትና ማለት ክርስቶስን መምሰል ነው፡፡ ክርስቶስን መምሰላችን መታወቂያው እና ማረጋገጫው የሐዋርያት ትምህርት ነው፡፡

ወገኖች ሆይ፥ የወርቅ ጥራቱ በካራት እንዲለካ፥ የዕቃ ክብደቱ በሚዛን እንዲለካ፥ ርዝመትና ስፋት፥ ከፍታና ጥልቀት በሜትር እንዲለካ፥ የክርስትናችን ጥራት፥ ክብደትና ጤና በሐዋርያት ትምህርት ይለካል፡፡

ታውቃላችሁ፥ ቡና ወርዶ ወርዶ አተላ እንዲሆን፥ ክርስትና ወርዶ ወርዶ ለሐዋርያት ትምህርት አለርጂክ ይሆናል፡፡ ሕግ ተላላፊ ፖሊስ እንዲፈራ፥ ክርስትናን ተላላፊ ሐዋርያትን ይፈራል፡፡

No comments:

Post a Comment