ዲቮሽን ቁ.61/07 ሰኞ፣ ሕዳር
1/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
አሮጌው
ሲጣፍጥ !
አሮጌ የወይን ጠጅ ሲጠጣ አዲሱን የሚሻ ማንም የለም፤
አሮጌው ይጣፍጣል ይላልና(ሉቃ 5፡39)።
ጌታን ስንቀበል የአሮጌ
ሰዋችንን ልማዶች እርግፍ አድርገን ጥለን አዲስ ሕይወት ጀምረናል! የጌታን መንገድ ስንከተል አሮጌ ልማዶቻችንን፣ ማለትም ስካር
ዘፋኝነቱን፣ ዝሙት እርኩሰቱን፣ መዳራት ጣዖቱን፣ ጥላቻ አለመግባባቱን፣ ቅናት ራስ ወዳድነቱን፣ አድመኝነት መለያየቱን፣ ምቀኝነትና
የመሳሰሉትን ጥለን ወጥተናል!
ወገኖች ሆይ፣ አንዳንዴ
አሮጌ ነገር ያምረናል! አንዳንዴ የድሮ ትዝታ፣ የድሮው ሁኔታ ይመጣብናል! አልፎ አልፎ አሮጌው ሰዋችን አሮጌውን ፈልጎ ይነሆልላል!
አንዳንዴም
አሮጌው ሰዋችን በአሮጌ
ሥራ ጠልፎ ይጥለናል!
ወገኖች ሆይ፣ አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ
አቁማዳ ማኖር እንደሚገባ፣ አዲስ ሰውነታችን በአዲስ ሕይወት ኑሮ መጠበቅ ይገባል! አሮጌው ልምምድ፣ አሮጌው ትዝታ፣ በጌታ
ያገኘነውን አዲስ ሕይወት እንዳይጎዳ በጸሎት እንትጋ!
ወገኖች ሆይ፣ የአሮጌው ዘመን ልማድ መልሶ
እንዳይዘን፣ የአሮጌው ዘመን መንገድ ዞሮ እንዳይገጥመን ጥንቃቄ እናድርግ! የዓለማዊነት ሕይወት ሊስበን ሲጀምር፣ የቀደመው
ነገር ሊያጠምደን ሲሞክር በጊዜ እንንቃ! ከቀድሞው ልምምድ፣ ከምኞት ቀጠና፣ ከሥጋ ፈተና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ በጾምና ጸሎት
በፍጥነት እንውጣ!
-------------------------
(እባክዎ፣ ይህን
ዕለታዊ
ዲቮሽን
ላይክ ያድርጉ፣
ወዳጅ ጓደኞችዎም እንዲያገኙ ያግዙ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!)
No comments:
Post a Comment