ዲቮሽን ቁ.78/07
ሐሙስ፣ ሕዳር 18/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን
ሐጢያ)
ከሥጋና ከደም ጋር መማከር!
ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ
እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና
ከደም ጋር አልተማከርሁም(ገላ 1፡15-16)
ወደዚህ ምድር ከመምጣታችን አስቀድሞ፣ ገና በእናታችን ማህጸን ሳለን፣ ጌታ
ያውቀናል፡፡ ከዚህ እውቀቱም የተነሳ ጸጋ ይሰጠናል፡፡ በዚህ ጸጋ እንድናገለግለውም ይጠራናል፡፡ በሚጠራን ጸጋና አገልግሎት ደግሞ
ልጁ ኢየሱስ እንዲገለጥ ይፈልጋል፡፡ ኢየሱስ በሕይወታችን እንዲገለጥ ወድዶ ጌታ ከጠራን፣ እንግዲያውስ ከሥጋና ደም (ራዕይ አጨንጋፊ
ሰዎች) ጋር መማከር አይገባም!
ወገኖች ሆይ፣ በኢትዮጵያ አብያተክርቲያናት ውስጥ ራዕይ አጨንጋፊ ሰዎች በዝተዋል! የተቀቡ
ሲነሱ ተጋግዘው የሚደቁሱ፣ ነቢያት ሲነሱ ተረዳድተው የሚያጨነግፉ በዝተዋል! ሐዋሪያት ሲወለዱ
ተረባርበው የሚያወግዙ፣ ሰባኪዎች ሲነሱ ተባብረው የሚነቅፉ ሞልተዋል!
ታውቃላችሁ፣ የሥነመለኮት ተቋማት የብዙዎቹን ጸጋ ላጭተዋል! ሐይማኖታዊ
ፍልስፍናዎች የእምነት ኃያላንን ቀርጥፈው በልተዋል! ክብሩን እንዲገልጡ የተጠሩ ብዙዎች ከኮሌጅ ሲገቡ ከሰው ይማራሉ! ክህደት፣
ጥርጣሬ፣ ጥያቄና ፍርሃት ለብሰው ይወጣሉ!
ወገኖች ሆይ፣ ከሐዋሪያ ጳውሎስ እንማር! እግዚአብሔር
ሲጠራው፣ ጠርቶም ሲቀባው፣ ከቴኦሎጂ ተቋም ለመማር አልገባም! የተቀበለውን ራዕይ ወደጎን አድርጎ፣ ከሥጋና ደም ጋር አልተመካከረም! ትምህርት ቤቶቻችን ይላጩ እንደሁ እንጂ ጸጋን አይጨምሩም፡፡ ፈተና ሲሰጡን፣
አሳይመንት ሲሰጡን ጭንቅላትን እንጂ የልብን አያውቁም!
ታውቃላችሁ፣ ትምህርት ቤቶቻችን የመመረቂያ እንጂ የመዳንን ራስ ቁር በእኛ ላይ
አይጭኑም! በጸሎት ሕይወት፣ በጸጋ አገልግሎት፣ በእምነት ትምህርት ውጤት ድካም አሳይተን፣
‹‹ብቁዎች ተብለን›› እንመረቃን፡፡ ሆኖም በምረቃ ዕለት የምንለብሰው ነገር ጥቁር ጋዋን እንጂ የጽድቅ ጥሩር አይደለም!
--------------------------------
(ትምህርቱ
ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክና ሼር
ያድርጉ፣ ወዳጅ ጓደኞችም እንዲያገኙ ያግዙ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!)
No comments:
Post a Comment