ዲቮሽን ቁ.70/07 ረቡዕ፣ ሕዳር
10/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
ሁሉን
በሚችል– አምናለሁ !
እኔ ሁሉን በሚችል – ምድረበዳን ወደገነት በሚቀይር፣ ከባዶ ነገር(ባራ)
ሕይወት በሚፈጥር፣ ድቅድቅ ጨለማ ላይ ብርሃን ይሁን በሚል፣ ምንም በማይሳነው በኤልሻዳይ ጌታ በእግዚአብሔር አምናለሁ፡፡
ደግሞም ከእርሱ ዓይኖች ፊት የሚሰወር ነገር፣ ገበናና ሚስጥር፣ ጨለማና
ግርዶሽ ችግር እንቆቅልሽ እንደሌለ አምናለሁ፡፡
ደግሞም ሁሉን ቻዩ ጌታ አንድን ቤተሰብ ከአንድ ግለሰብ፣ ትልቁን ጉባኤ
ከትንሹ አጥቢያ፣ ወንዱን ከሴቱ፣ ወጣቱን ከአዛውንቱ፣ ደካማን ከብርቱ እንደማያበላልጥ፣ እንደማይመርጥ፣ እንደማያዳላና እንደማይጠላ
አምናለሁ፡፡
ደግሞም፣ ከባሕል ከደንባችን ውጭ፣ ከወግ ከልማዳችን ውጭ፣ ከእውቀት ከግንዛቤያችን
ውጭ፣ ከፍልስፍና ከመላምታችን ውጭ፣ ከበጀት ከፎርሙላችን ውጭ መሥራት እንደሚችል አምናለሁ፡፡
ደግሞም፣ ሐዋርያት ሊያስነሳ፣ ነቢያት ሊቀባ፣ ፈውስና ተአምራት፣
ድንቅና ምልክት፣ ያልተለመደና አነጋጋሪ ነገር ሊያደርግ እንደሚችል
ደግሞም፣ እርሱ እንደወደደ በዘይትና ቅባት፣ በጨርቅና ውሃ አልፎ
እንደሚሠራ አምናለሁ፡፡
ደግሞም እርሱ እንደፈቀደ በምሁር በማይም፣ በድንጋይ በአህያ መጠቀም
እንደሚችል አምናለሁ፡፡
ደግሞም፣ ከሰማያት መናን፣ ከመካኒቱ ልጅን ከድሃው ብልጥግናን በረከትና
ሀብትን ማዝነብ እንደሚችል አምናለሁ፡፡
ደግሞም፣ ሊገድል–ሊያድን፣ ሊያወጣ–ሊያወርድ፣ ሊጥል–ሊያነሳ፣ ሊሰጥ–ሊነሳ፣
ሊያጎድል–ሊያበዛ፣ ሊያሳዝን–ሊያጽናና፣ ሊያከብር–ሊያዋርድ፣ ሊፈውስ–ላይፈውስ፣ ሊያበለጽግ–ሊያደኸይ በሚችል በሁሉን ቻይ
አምላክ በእግዚአብሔር አምናለሁ፡፡
No comments:
Post a Comment