Friday, October 17, 2014

ሸካይና!

ዲቮሽን ቁ.37/07     አርብ፣ ጥቅምት 7/07 ዓ.ም.  
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)


ሸካይና!

…ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ልብሱም አንጸባረቀ፤… ደመናም መጥቶ ጋረዳቸው፥ ከደመናውም። የምወደው ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ (ማር 9፡28-35)

ጸሎት የጌታን ክብር (ሸካይና) ይገልጣል! የጸሎት ከፍታ ሞገሱን ያሳያል! የጸሎት ተራራ የእግዚአብሔርን ድምጽ ያሰማል!

ወዳጄ ሆይ፣ በሕይወትዎ ክብሩን ማየት፣ ድምጹን መስማት ይናፍቃሉ? እንግዲያውስ፣ ወደ ተራራ ይውጡ! ከእምነት ተራራ፣ ከጸሎት ተራራ! ከመንፈስ ከፍታ መውጣት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ፣ ከሸለቆ ይውጡ፣ ከኃጢአት ሸለቆ፣ ከእርኩሰት ሸለቆ፣ ይውጡ! ከጣዖት ሸለቆ፣ ከዓለም ሸለቆ፣ ከሰይጣን ሸለቆ ይውጡ!

ወዳጄ ሆይ፣ ጥርት ያለ ድምጹን መስማት ከፈለጉ፣ የእምነት አንቴና፣ ቻናል ያስተካክሉ! ጥርት ያለ ራዕይ ማየት ከፈለጉ፣ እንቅልፍ ያስወግዱ! የመጥራቱን ተስፋ፣ የብርታቱን ጉልበት፣ የኃይሉን ታላቅነት ማወቅ ከፈለጉ፣ ጌታ ወዳየልዎ ከፍታ ላይ ይምጡ! የባለጠግነትዎትን መጠን፣ የርስትዎትን ወሰን ማየት ከፈለጉ፣ ጌታን ተከትለው ከፍታ ላይ ይውጡ! ሌላ ጣቢያ ዘግተው እርሱን ብቻ ይስሙ!

 ሸካይናውን ማየት፣ ድምጹን መስማት ይሁንልን! መንፈሳችን ነቅቶ፣ ዓይናችን ተከፍቶ ያየልንን ማየት ያዘዘንን መስማት ይሁንልን!

---------------------------
ማስታወቂያ፣

(1) ጌታ ቢፈቅድ፣ ከመስከረም 1 እስከ ሕዳር 30/07 ያለው ዕለታዊ ዲቮሽን በመጽሐፍ ታትሞ ኢንተርኔት ለማይጠቀሙ ሐበሾች የማድረስ ራዕይ አለኝ፡፡ ስለሆነም፣ ይህን ራዕይ በገንዘብ በመደገፍ አገልግሎቱን ለማሳደግ ልባችሁ የተነሳሳ ወገኖች አነሰ በዛ ሳትሉ የእምነት ዘር በመዝራት ከጎኔ እንድትቆሙ በጌታ ፍቅር እጠይቃለሁ፡፡ የፍቅር ስጦታችሁን (Tesfahun Hatia Daka, Commercial Bank of Ethiopia, Andinet Branchl; A/C 1000036318949; 
Swift Code: CBETETAA) በማለት መላክ ትችላላችሁ፡፡ ለዘሪ ዘርን የሚሰጥ ጌታ ዘራችሁን ይባርክ!

(2) ጌታ ቢፈቅድ ከአዲሱ የፈረንጆች ዓመት 2015 ጀምሮ፣ ከአማርኛው ዕለታዊ ዲቮሽን በተጨማሪ፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ዕለታዊ ዲቮሽን እጀምራለሁ፡፡ ይህ አገልግሎት በመላው ዓለም የሚገኙ የእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚግባቡትን ሁሉ ለመድረስ ኢላማ ያደረገ ነው፡፡ ስለሆነም፣ በጸሎታችሁ እንድታስቡኝ በጌታ ፍቅር አደራ እላለሁ፡፡


(3) ‹‹የወንጌላዊው እጮኛ›› በሚል ርዕስ የተዘጋጀና በወንጌል አገልጋዮች ላይ የሚያጋጥሙ እውነተኛ ልብ አንጠልጣይ ታሪኮችን አሰባስቦ የያዘ መጽሐፍ ጌታ ቢፈቅድ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ለንባብ ይበቃል፡፡ ይህን መጽሐፍ በመግዛት ዕለታዊ ዲቮሽኑን እንድትደግፉ በአክብሮት እየጠየቅሁ፡፡ በአገር ውስጥ ያላችሁም ሆነ ከአገር ውጭ መጽሐፉን በመን መንገድ ልልክላችሁ እንደምችልም መረጃ እንድትሰጡኝ በአክብሮት አሳስባለሁ፡፡ የመጽሐፉ መሸጫ ዋጋ በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ ይሆናል! ጌታ ይባርካችሁ! 



No comments:

Post a Comment