ዲቮሽን
244/07፣ ማክሰኞ፣
ግንቦት
4/07
(በወንድም ጌታሁን ሓለፎም)
ትንቢታዊ መልዕክት!
ባንድም በሌላም መንገድ መሥራት የማያቅተው ጌታ ፤ በጥቂቱም በብዙም ማዳን የማይሳነው ኢየሱስ ዛሬ የጠራሁት ህዝቤ በዚህ ቃል ይጽናና አለኝ !
“ኢያሪኮም ከእስራኤል ልጆች የተነሳ ፈጽማ ተዘግታ ነበር፤ ወደ እርሷ የሚገባ ከእርሷም የሚወጣ
ማንም አልነበረም። እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው ። ተመልከት፤ እያሪኮን እና ንጉሱዋን ጽኑአን ኃያላንዋንም በእጅህ ሰጥቼህ አለሁ (ኢያ 6፡-1-2)።
ቆይ ! ለመሆኑ ነገሮችዎ ጥርቅምቅም ብለው የተዘጉበት ምክንያት፤ ጥብቅብቅ ብለው የተቆለፉበት ሰበቡ ምን እንደሆነ ያውቃሉ?
እግዚአብሔር በቃሉ ያጸናልዎት፤ ጌታ በመንፈሱ ያተመልዎት ‹‹ይሆናል፤ ይሳካል፤ ትወርሳለህ፤ ታየዋለህ፤ ትከናወናለህ›› የተባለልዎት በእውነተኛ የትንቢት ቃል የተነገረልዎት ነገሮችዎ ድርቅ ብለው አንድ ቦታ ላይ የቆሙበት፣ ዝም፣ ጭጭ፣ እረጭ ያሉበት ምክንያት ለምን እንደሆነ ያውቃሉ?
ነገሩ እንዲህ ነው ኢያ 6፡-1ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ኢያሪኮም ከእስራኤል ልጆች የተነሣ ፈጽማ ተዘግታ ነበር፡፡›› ከማን የተነሳ ተዘጋች? ‹‹ከእስራኤል ልጆች የተነሳ›› ማንም ሲወጣባት፣ ሲገባባት የነበረችዋ ኢያሪኮ በሮቿ ደጆቿ ለዎትሮው ተከፋፍተው የሚውሉት ኢያሪኮ አሁን ጥርቅምቅም፣ ዝግትግት አሉ፡፡
ግን ለምን?
የኢያሪኮ ግንብ ዝግትግት፣ ጥርቅምቅም ማለቱ፣ አላስገባም አላስወጣም ብሎ መከርቸሙ ለምን እንደ እንደሆነ አሁን አስተዋሉ? እስራኤልን ፈርቶ እኮ ነው! ማር እና ወተት የምታፈሰውን ምድሯ ከሰማይ ጠል የምትረሰርሰውን እግዚአብሔር ያዘጋጃት ከንአንን ትወርሳለህ የተባለለትን ኢያሱን ፈርታ እኮ ነው!!
አዩ አሁን ቅዱስ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሊወርሳት ነው! የተለየ ሕዝብ ሊገባባት ነው! የተመረጠ የእግዚአብሔር ህዝብ ሊቆጣጠራት ነው! በውስጧ ያለው እርኩሰቷ፣ ክፋቷ ሊቆረጥ ነው! አስማት መተቷ ጥንቆላ ሟርቷ ሊገለበጥ ነው! ስለዚህ እያሪኮ ተጨነቀች በዚህም ምክንያት ደጆቿ ተቆላለፉ፣ ማንም እንዳይወጣ፣ ማንም እንዳይገባ ሳንቃዋ ተከረቸመ!
አዩ! ከእግዚአብሔር የተነገረልዎት፣ እርስዎ እጅ የሚገባው ብልጽግና አሁን ስርአት ሊይዝ ነው!
ሰይጣን ለጥፋት የሚጠቀምበት የምድር በረከት እርስዎ እጅ ሲገባ ሊቀደስ ነው! ስለዚህ እርስዎ እጅ እንዳይገባ ባለበት ድርቅ፣ ክርችም ቁልፍልፍ ይላል፡፡
ግን ጌታ ምን እንደሚያደርግ ልንገርዎ፡፡ ኢያ 6፡-2 ‹‹እግዚአብሔርም እያሱን አለው፣ ተመልከት ኢያሪኮንና ንጉሥዋን፣ ጽኑአን ኃያልንዋንም በእጅህ ሰጥቼህለሁ፤ ተመልከት፤ አይንህን ግለጥ፤ እይ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፡፡››
አንተ የተወደድክ የልዑል እግዚአብሔር ሕዝብ ሆይ፣ አትፍራ!
አንገትህን አታቀርቅር፣ በተዘጋው በተቆለፈው ነገርህ ላይ ቀና በልበት፤ ደረትህን ነፋ፣ አይንህን ግልጥ ኮስተር በልበት፤ ተመልከተው ጌታ አምላክህ አሳልፎ ሰጥቶሃል!
‹‹ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅእት ናት፡፡›› ሉቃ 1፡-45
በትንቢታዊ መልዕክቱ ተጽናንተዋል? እንግዲያውስ
ላይክ ያድርጉ፣ ጌታ ይባርክዎ!
No comments:
Post a Comment