ዲቮሽን ቁ.176/07፣ ሐሙስ፥ የካቲት 26/07 ዓ.ም.
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
ጎልያዶቻችን!
ዳዊትም ሳኦልን፦ ስለ እርሱ የማንም ልብ አይውደቅ፣ እኔ ባሪያህ
ሄጄ ያንን ፍልስጥኤማዊ እወጋዋለሁ አለው (1 ሳሙ 17፡32)።
ብዙ ጊዜ በአማኝ ሕይወት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ትናንት እና
ከትናንት በስቲያ ካጋጠሙን ተግዳሮቶች ይልቅ የከበዱና የተለቁ ናቸው፡፡ አጋጥመውን ከሚያውቁ ተግዳሮቶች ይልቅ የቀለሉና ያነሱ ከሆነ፣
እነርሱ የተሸነፉ ተግዳሮቶች ስለሆኑ ቀንደኛ ተግዳሮት መሆናቸው ይቀራል!
ወገኖች ሆይ፣ አጋጥመውን የማያውቁ የከበዱና የተለቁ ተግዳሮት
ሲመጡ እምነታችን የምር በአዲስ የፈተና ሚዛን ላይ ይቀመጣል! በዚህ ፈተና አሸንፎ መውጣት ግን በእግዚአብሔር ላይ ባለን እምነት
ላይ የተወሰነ ይሆናል!
ወገኖች ሆይ፣ ዳዊትን አስቡ! ዳዊት በበግ እረኝነቱ ሥራ ላይ
የአንበሳና የድብ ጥቃት፣ የጠቦቶች ንጥቂያ ያጋጥሙት ነበር፡፡ እነዚህን አራዊት በወንጭፍና ድንጋይ መከላከል የለመደ ወጣት ነበር፡፡
ነገር ግን እንደ ጎልያድ ያለ ከአንበሳና ከድብ ይልቅ እጅግ የከበደና የተለቀ ተግዳሮት አጋጥሞት አያውቅም! በጦር የሰለጠነና የታጠቀ
አውሬ አጋጥሞት አያውቅም፡፡
ታውቃላችሁ፣ ዳዊት እንዲህ ያለ ችግር፣ እጅግ የከበደ እጅግ
የተለቀ ተግዳሮት ተግዳሮት አጋጥሞት ባያውቅም፣ ከእግዚአብሔር ጋራ አጋጥሞት የማያውቀውን ይህን የከበደና የተለቀ ተግዳሮት አሸንፎ
እንደሚወጣ አልተጠራጠረም፡፡ በትናንትናው ሰልፍ፣ በትናንቱ ተግዳሮት አብሮት የነበረው የእግዚአብሔር ክንድ ባልለመደው ትግል በማያውቀው
ሰልፍ ውስጥ ድል እንደሚሰጠው እርግጠኛ ነበር፡፡
ታውቃላችሁ፣ የትናንትናዎቹ አውሬዎች ድብና አንበሶች በእግዚአብሔር
ተመትተው ወድቀው አይቷልና የዛሬውም አውሬ ተመትቶ እንደሚወቅድ አልተጠራጠረም፡፡ ጎልያድ ምንም ግዙፍ ቢሆን፣ ጋሻ ጦርና ሰይፍ
የታጠቀም ቢሆን በሰዎች ዓይን ሲታይ ምንም ቢያስፈራ፣ ዳዊት ከወንጭፉ ከድንጋዩ ሌላ ምንም አልታጠቀም!
ታውቃላችሁ፣ ትናንት ከትናንት በስቲያ ከታጠቀ ጠላት፣ ከሚያጠፋ
እሳት፣ ከሚያሰጥም ውሃ፣ ከሚውጠን ጉድጓድ፣ ከውርደትና ጉድ ሊያድነን የቻለ፣ ብቻውን ተአምራት የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ ዛሬም
በዙፋኑ፣ ዛሬም በችሎታው ዛሬም ከእኛ ጋር አለ! ወዳጄ፣ በጎልያድዎ ወይም በተግዳሮትዎ ግዝፈት ልብዎ አይውደቅ!
ወዳጄ ሆይ፣ ትናንት፣ ከትናንትም በስቲያ ያልለመዱት ውጊያ፣
ያላወቁት ትግል፣ እጅግ የከበደና የተለቀ ተግዳሮት ቢያጋጥምዎ፣ ትናንት ከትናንትም በስቲያ አብሮዎት የነበረው ጌታ ዛሬም ይረዳዎታልና
ሳይጠራጠሩ፣ በጌታ ተማምነው ጎልያድን ይግጠሙ!
--------------------------------
(ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፣ ጌታ ይባርክዎ!)
(1) ኤግል የሬዲዮ አገልግሎት በአማርኛ ቋንቋ መጀመሬን
በደስታ አሳውቃለሁ፡፡ በየትኛውም ዓለም የሚገኙ አማርኛ አድማጮች
http://zenoradio.com/en/listeners/ET/Eagle+Amharic+Radio/
በመጫን ሊያዳምጡ ይችላሉ፡፡ አሜሪካና ካናዳ የሚኖሩ በነጻ ስልክ (605) 562 4274 ማዳመጥ ይችላሉ፡፡
(2) ዲቮሽኖቹን በብሎግ ለመከታተል የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ https://draft.blogger.com/blogger.g?blogID=7832170107481561272#allposts
No comments:
Post a Comment