Wednesday, January 21, 2015

መልካም ይሆንልሃል !

ዲቮሽን .133/07     ረቡዕጥር 13/07 ..
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)


መልካም ይሆንልሃል

የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና ጻድቁን፦ መልካም ይሆንልሃል በሉት (ኢሳ 1፡10)፡፡

ሰው የዘራውን ያጭዳል፡፡ ኃጢእ ኃጢአትን ዘርቶ ኃጢአት እንደሚያጭድ፣ ጻድቅ ጽድቅን ዘርቶ ጽድቅን ያጭዳል፡፡ ጻድቅ መልካም ዘር ይዘራል፣ በጎነት፣ ቸርነት፣ ይዘራል፣ ይህንኑ ያጭዳል፡፡  

ወገኖች ሆይ፣ ጻድቅ እምነትና ተስፋ ፍቅርና ደስታ ይዘራል፣ ይህንኑ ያጭዳል! ጻድቅ በረከት ይዘራል፣ በረከትን ያጭዳል! ጽድቅን የሚከተል የጽድቅ ፍሬ ያጭዳል!

ወገኖች ሆይ፣ ጻድቅ ስለ ወደፊቱ ኑሮ ሊፈራ አይገባም! ምክንያቱም የእንባውን ዋጋ፣ የልፋቱን ብድራት፣ የድካሙን ክፍያ በእጥፍ ይቀበላልና፡፡ ጻድቃን በኃጢአተኞች መካከል እየተመላለሱ፣ ነገር ግን በዓለም እርኩሰት ሳይዘፈቁ በጽድቅ ስለሚኖሩ፣ ስደት ይደርስባቸዋል፡፡

ወገኖች ሆይ፣ በጽድቅ ሥራ ምክንያት በመልካም ሥራቸው ዓለምን እየኮነኑ፣ በፈርሃ እግዚአብሔር በጽድቅ ሲመላለሱ መከራ ይደርባቸዋል! ስለሆነም፣ ጻድቃን መልካም ነገር ያገኛሉና ይህን እንንገራቸው! ለጻድቃን ሁሉ መልካም ነገር ሁሉ ይገጥማቸዋልና፣ ይህን እንንገራቸው!

ወገኖች ሆይ፣ ጻድቃን የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና ይህንኑ እውነት እንገራቸው፡፡ በሚደርስባችሁ ጫና፣ በሚርስባችሁ ፈተና ተስፋ አትቁረጡ፣ አይዟችሁ፣ መልካም ይሆንላችኋል እንበላቸው! በሚገጥማችሁ ችግር፣ በሚደርስባችሁ ስደት ተስፋ አትቁረጡ፣ መልካም ይሆንላችኋልና አይዟችሁ እንበላቸው!  

ወገኖች ሆይ፣ ጻድቃን ሆይ፣ ብድራታችሁ ከላይ ነውና፣ የጽድቃችሁ ዋጋ  ይከፈላችኋልና፣ አይዟችሁ፣ መልካም ይሆንላችኋል እንበላቸው!  

-----
ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!

No comments:

Post a Comment