ዲቮሽን
ቁ.105/07 ረቡዕ፣ ታህሳስ 15/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
ነፍስን
መካድ!
ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት
እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ
(የሐዋ 20፡24)።
እውነተኛ አማኞች ከጌታ ከኢየሱስ ወንጌልን የመመስከር አገልግሎት
ተቀብለዋል፡፡ ይህ አገልግሎት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ እስከ ይሁዳ፣ ሰማሪያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ መሮጥ ይጠይቃል፡፡ ይህን ሩጫ
ለማድረግ ስንጥር ግን፣ መከራና ፈተና እንዲሁም እስራት ይጠብቀናል፡፡ የታላቁ ተልዕኮ ሩጫ፣ ራስን መካድን፣ ነፍስን በእኛ ዘንድ
እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር መቁጠርን ይጨምራል፡፡
ወገኖች ሆይ፣ ነፍሱን የሚወድድ ሰው ታላቁን ተልዕኮ በብቃት
ለመወጣት ይቸግረዋል! የሚጠፉ ነፍሳትን ለማዳን የራስን ነፍስ መቁረስ አስፈላጊ ይሆናል!
የራስን ነፍስ ስንቆርስ የሌሎች ነፍስ ይድናል፡፡ ሌሎች እንዲኖሩ መሞት ይጠይቃል፡፡ ሌሎች እንዲድኑ ራስን መስጠት የግድ ይላል፡፡
ራስን መስጠት ምርኮ ያበዛል፡፡
--------------------------------
‹‹የወንጌላዊ
እጮኛ›› በሺዎች የተደነቀ ልብ አንጠልጣይ መጽሐፍ እሁድ፣ ታህሳስ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡00 ይመረቃል፡፡
ካዛንቺስ ኡራኤል መካነየሱስ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት እንዲገኙልኝና ይህንን
ታሪካዊ መጽሐፍ እንዲመርቁልኝ በአክብሮት ጋብዤዎታለሁ፡፡
No comments:
Post a Comment