ዲቮሽን ቁ.55/07 ማክሰኞ፣ ጥቅምት
25/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
በፊትህ
የሚሄድ!
እግዚአብሔር ራሱ በፊትህ
ይሄዳል፤ ከአንተም ጋር ይሆናል፤ ፈጽሞ አይለይህም፤ አይተውህምም፤ አትፍራ፤ ተስፋም አትቁረጥ (ዘዳ 31፡8)
የሰው ልጆችን እጅግ
ከሚያሳስቡና ከሚያሰጉ ነገሮች መካከል አብሮ የሚኖር ወዳጅ ጓደኛ ማግኘትና ማጣት፣ ከወዳጅ ጓደኛ መለየት፣ መተውና መረሳት፣ እንዲሁም
ፍርሃት ናቸው፡፡
ወገኖች ሆይ፣ ‹‹በፊትህ
የሚሄድ እርሱ እግዚአብሔር ነው›› የሚል ሐረግ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ከ1995 ጊዜ በላይ ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡ ይህን ወደ
ዓመቱ ቀናት ብናካፍል ለእያንዳንዱ ቀን ከ5.5 ጊዜ በላይ ይደርሰዋል ማለት ነው፡፡
ወገኖች ሆይ፣ በእውነተኛ
አማኞች ፊት እግዚአብሔር በማለዳም፣ በቀትርም፣ በተሰዓትም በቀንና በለሊት በፊታቸው ይሄዳል! እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣብቀን
ከሆነ፣ የሙጥኝ ይዘነው ከሆነ፣ የእግዚአብሔር አብሮነት ከእኛ ጋር ነው! እግዚአብሔር ፈጽሞ አይለየንም፤ ፈጽሞ አይጥለንም፣ ፈጽሞም
አይተወንም!
ወገኖች ሆይ፣ ‹‹አትፍራ››
የሚል ቃል በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ከ365 ጊዜ በላይ ተጠቅሶአል ሲባል ሰምተናል፡፡ በእያንዳንዱ ዕለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር
ስለሆነ ልንፈራ አይገባም! በዙሪያችን ብዙ የሚያስፈሩ ነገሮች ቢኖሩም ግርማው የሚያስፈራ ጌታ ከእኛ ጋር ነውና አንፍራ! እግዚአብሔር
ከእኛ ጋር ከሆነ የሚያስፈራው አይወርሰንም!
ወገኖች ሆይ፣ ተስፋ
የሚያስቆርጡ ብዙ ነገሮች በዙሪያችን ቢኖሩም ጌታ ግን አብሮን ነው! ተስፋችንን በእግዚአብሔር ላይ እናድርግ! እርሱ የማይሰበር
ምርኩዝ ነውና ጌታን ተስፋ እንድርግ! እግዚአብሔር የሚሰጠው ተስፋ ፈጽሞ አይወድቅምና በእግዚአብሔር እንታመን! ተስፋ ቃል ከሰጠ
እግዚአብሔር ታማኝ ነው!
ወዳጄ ሆይ፣ እግዚአብሔር ራሱ በፊትህ ከሄደ ይባርክሃል፥ ይጠብቅሃል፣ ፊቱን ያበራልሃል፣ ይራራልሃል፣ ፊቱን ወደ አንተ ያነሣል፥ ሰላምንም ይሰጥሃል፡፡ እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፣ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፣ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ (ዘሁ 6፡24-26)።
-------------------------
(ይህን
ዕለታዊ
ዲቮሽን
ላይክና ሼር ያድርጉ፣ ወዳጅ ጓደኞችዎም
እንዲያገኙ
ያግዙ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!)
No comments:
Post a Comment