ዲቮሽን ቁ.54/07 ሰኞ፣ ጥቅምት
24/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
ደመናዎን
ይጠብቁ!
ደመናው
በተነሣ ጊዜ በቀንም በሌሊትም
ቢሆን፥ ደመናው በተነሣ ጊዜ
ይጓዙ ነበር። ደመናውም ሁለት ቀን ወይም አንድ ወር ወይም አንድ ዓመት ቆይቶ በማደሪያው ላይ ቢቀመጥ የእስራኤል ልጆች
በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር፤ ነገር ግን በተነሣ ጊዜ
ይጓዙ ነበር። …ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ።
አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ ይል ነበር። (ዘሁ 9፡16-35)
መንፈሳዊ ሰው ከዓለማዊው
ከሚለይባቸው መንገዶች አንዱ የጌታን ፈቃድ ማወቅና ጊዜውን ጠብቆ መውጣት ነው! ይህም ማለት ወቅታዊ ምሪት ከጌታ መቀበልና መሰማራት
ነው ! ከዚህ በፊት ‹‹ወቅታዊ
የምሪት
ቃል–ካይሮስ-ሬማ›› በሚል የተማማርነውን ልብ ይሏል!
እስራኤላዊያን ወደ ተስፋዪቱ ምድር ሲጓዙ የእግዚአብሔርን ምሪት አጥብቀው ይከተሉ ነበር! እግዚአብሔር
ሕዝቡን ቀን ቀን–በደመና አምድ፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ–በእሳት አምድ ይመራቸው ነበር! ደመናው ሲነሳ ይነሣሉ! ሲቆም ይቆማሉ!
ሲሰነብት ይሰነብታሉ!
እግዚአብሔር ሲነሳ ይነሳሉ፣ ሲቆም ይቆማሉ! እስራኤላዊያን ምሪቱን ተከትለው ይንቀሳቀሳሉ ማለት
ነው! እስራኤላዊያን በምሪት ይንቀሳቀሱ ስለነበረ፣ ከፊታቸው ያሉት የእግዚአብሔር ጠላቶች ይበተኑ፣ ይሸሹም ነበር!
ታውቃላችሁ፣ ደመና ጠብቀን፣ በምሪት ስንወጣ ከፊታችን እግዚአብሔር ይሄዳል! እግዚአብሔር ከፊታችን ካለ ደግሞ ከፊታችን ያለ ማንኛውም ሰልፍ ይበተናል!
እግዚአብሔር ቀድሞን ከወጣ ከፊታችን ያሉ ጠላቶቻችን ይሸሻሉ! ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይበንናሉ! ሰም በእሳት ፊት
እንደሚቀልጥ እንዲሁ ይቀልጣሉ!
ታውቃላችሁ፣ በምሪት ከወጣን ሰማይ መና ያዘንባል! በምሪት ከወጣን ምድረበዳው ምንጭ ያፈልቃል! ተራራ
ይናዳል፣ ባህር ይከፈላል፣ እንቅፋት ይፈርሳል! ጠብቀን ከወጣን ታሪክ ይለወጣል! ስለሆነም፣ ደመናችንን እንጠብቅ! ደመና ካላየን፣
ጌታ ካልቀደመን–አንውጣ ይቅርብን!
-------------------------
(ይህን
ዕለታዊ
ዲቮሽን
ላይክና ሼር ያድርጉ፣ ወዳጅ ጓደኞችዎም
እንዲያገኙ
ያግዙ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!)
No comments:
Post a Comment