ዲቮሽን ቁ.74/07 እሁድ፣ ሕዳር
14/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
እግዚአብሔርን መናቅ!
እግዚአብሔር
እንዲህ ይላል፦ የሚያከብሩኝን አከብራለሁ፤የሚንቁኝም ፈጽሞ ይናቃሉ፡፡ (1 ሳሙ 2፡30)
አንዳንድ
አገልጋዮች እግዚአብሔርን በሥራቸው ሲንቁ ይታያል! በጎደፈ ሕይወት እየተመላለሱ፣ ነውረኛ መስዋዕት እያቀረቡ፣ ያለ ፈርሃ
እግዚአብሔር እያለገሉ እግዚአብሔርን ይንቃሉ! ምሕረቱን–ትዕግሥቱን፣ ችሎታ–ብቃቱን፣ ኃይልና–ሥልጣኑን
ይንቃሉ! የተፈራ ስሙን፣ ጽድቁን–ቅድስናውን፣ ክብሩንና–ፍርዱን ይንቃሉ!
ወገኖች
ሆይ መጋቢዎች እግዚአብሔርን ይንቃሉ! ምናምንቴ ቍርባን ፊቱ እያቀረቡ፣ በአጸያፊ ዕጣን ቤቱን
እያገሙ፣ ያልተቀደሰ ነገር እየነካኩ፣ አደባባዮቹን በትዕቢት እየረገጡ፣ ጌታን ይንቃሉ!
ወገኖች
ሆይ፣ መሪዎች እግዚአብሔርን ይንቃሉ! ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ እያሉ፣ ጨለማውን ብርሃን
ብርሃኑንም ጨለማ እያደረጉ፥ ጣፋጩን መራራ መራራውን ጣፋጭ እያደረጉ ጌታን ይንቃሉ!
ያልተቀደሰ ስብሰባ እየተሰባሰቡ፣ ያልተፈወሰ አጀንዳ እየተነጋገሩ፣ የዐመጻ ፊርማ–የክፋት ውሳኔ እያስተላለፉ ጌታን ይንቃሉ!
ወኖች
ሆይ፣ ነቢያት እግዚአብሔርን ይንቃሉ! በዓይናቸው እያዩ–ዓይናቸውን ጨፍነው፣ በጆሮ እየሰሙ–ጆሮአቸውን
ዘግተው፣ ልባቸው እያወቀ–ልብን አደንድነው እየተመላለሱ ጌታን ይንቃሉ!
ወገኖች
ሆይ፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ እግዚአብሔርን ይንቃል! መስማትን እየሰማ ማስተዋል ተስኖት፣ ማየትን እያየ
መመልከት አቅቶት ጌታን ይንቃል!
ወገኖች
ሆይ፣ እግዚአብሔርን አንናቅ! እግዚአብሔርን መናቅ አደጋ ያመጣል!
እግዚአብሔርን መናቅ ላልታሰበ ስብራት፣ ላልተጠበቀ መዓት ያጋልጣል! ወገኖች ሆይ፣ በቃልና በሥራ እግዚአብሔርን እናክብር!
የሚያከብሩትን አክባሪ ነውና፣ እግዚአብሔርን እናክብር!
--------------------------------
(ከመስከረም
1/2007 ጀምሮ ዕለታዊ ዲቮሽን ፖስት በማድረግ ላይ ነኝ፡፡ ሁሉም ወዳጆቼ ትምህርቱ ጠቃሚ
ሆኖ ካገኙት፣ ላይክና ሼር እንዲያደርጉ፣ ወዳጅ ጓደኞቻቸውም መጠቀም እንዲችሉ እንዲያግዙ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ ይህ ዲቮሽን የመማማሪያ
መድረካችን እንዲሆን ፍላጎት አለኝ፡፡ ስለሆነም፣ ያልተብራራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ፣ ወይም ማግኘት የምትፈልጉት መንፈሳዊ ምክር
ካለ አቅርቡ፣ ጌታ እንደረዳኝ ለመመለስ እሞክራለሁ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!)
No comments:
Post a Comment