Monday, October 27, 2014

ወንድሞች ፍላጻ ሲወረውሩብዎ !



ዲቮሽን ቁ.47/07     ሰኞ፣ ጥቅምት 17/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)

ወንድሞች ፍላጻ ሲወረውሩብዎ !

የታላቅ ወንድሙ… የኤልያብ ቍጣ በዳዊት ላይ ነድዶ። ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂቶች በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውሃቸው? እኔ ኵራትህንና የልብህን ክፋት አውቃለሁና ሰልፉን ለማየት መጥተሃል አለው። ዳዊትም፦ እኔ ምን አደረግሁ? ይህ ታላቅ ነገር አይደለምን? አለ። ዳዊትም ከእርሱ ወደ ሌላ ሰው ዘወር አለ፥ (1 ሳሙ 17:28-30)


ወዳጄ ሆይ፣ ወንድሞች ፍላጻ ሲወረውሩብዎ ምን ያደርጋሉ? ባላጠፉት ነገር ወቀሳ ሲደርስብዎ፣ ባላወቁት ነገር ትችት ሲዘነዘርብዎ ምን ያደርጋሉ? ባልጠበቁት ነገር ስምዎ ሲጠፋ፣ ባልገመቱት መንገድ ውርደት ሲመጣ በእውነቱ ምን ያደርጋሉ? በሐሰት ሲከሰሱ፣ በውሸት ሲደቆሱ፣ በከንቱ ሲታሙ፣ በአሻጥር ሲገመገሙ፣ ቢቆስሉ ቢደሙ በእውነቱ ምን ያደርጋሉ? 

ወዳጄ ሆይ፣ ወንድሞች ፍላጻ ሲወረውሩብዎ ከዳዊት ይማሩ! ባላጠፉት ነገር ትችት ሲቀርብልዎ ሙግት አይግጠሙ! ከጥሪዎ መስመር ከዓላማ አይውጡ! ራስዎን እስካወቁ ጌታዎን እስካወቁ ለወሬ ፊት አይስጡ! ራስዎን ካወቁ፣ ጥሪዎን ካወቁ፣ ጌታዎን ካወቁ በሚቀርበው ትችት፣ በሚወርደው መዓት ትጥቅዎን አይፍቱ! ወሬን ፈርተው፣ ትችት ጠልተው ከፍታዎትን ለቅቀው ከመሬት አይውረዱ! ለወረደ ነገር ጆሮዎትን አይስጡ! ጌታን ብቻ ይስሙ፣ ጌታን ብቻ ይፍሩ! 

-------------------------
(ይህን ዕለታዊ ዲቮሽን ላይክና ሼር ያድርጉ፣ ወዳጅ ጓደኞችዎም እንዲያገኙ ያግዙ፡፡ ይህን አገልግሎት ለመደገፍ (Tesfahun Hatia Daka, Commercial Bank of Ethiopia, Andinet Branch; A/C 1000036318949; Swift Code: CBETETAA) መላክ ትችላላችሁ፡፡ ለዘሪ ዘርን የሚሰጥ ጌታ ዘራችሁን ይባርክልኝ!)

No comments:

Post a Comment