Saturday, October 25, 2014

ይራቁ!



ዲቮሽን .45/07 ቅዳሜ፣ ጥቅምት 15/07 ..
(
በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)


ይራቁ!


ወዳጆች ሆይ፣ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንደ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ (1 ጴጥ 1፡11)

ወዳጄ ሆይ፣ ነፍስዎን የሚዋጋ ሥጋዊ ፍላጎት አለ? ይራቁ ! በክርስቶስ የበራልዎትን ብርሃን ሊያጨልም የሚታገልዎ ነገር አለ? ይራቁ! በጌታ ያገኙትን እምነት የሚያራክስ፣ በመንፈስ ያገኙት ድፍረት የሚቀንስ ማናቸውም ዓይነት ሥጋዊ ነገሮች አሉ? ይራቁ!

ወዳጄ ሆይ፣ በጓደኛዎ፣ በቤተሰብዎ፣ በሥራ አለቃዎ ወይንም በማናቸውም አካላት በኩል ሕይወትዎ እንዲቆሽሽ የሚገፋፋዎት ኃይል አለ? ይራቁ! ሊያገኙ የሚመኙት፣ ሊወርሱ የሚያቅዱት፣ ሊጎናፀፉ የሚፈልጉት ነገር ግን ለሥጋዎ እንጂ ለነፍስዎ የማይጠቅም ነገር ይኖር ይሆን? ይራቁ!


ወዳጄ ሆይ፣ በክርስቶስ ደም ከታላቅ እስራት የተፋታችውን ነፍስዎ መልሶ ከሚዋጋ፣ ከሚያስርና ከሚቆጣጠር ማናቸውም ሥጋዊ ኃጢአት ራስዎን ይጠብቁ! 


-------------------------
(
ይህን ዕለታዊ ዲቮሽን ላይክና ሼር ያድርጉ፣ ወዳጅ ጓደኞችዎም እንዲያገኙ ያግዙ፡፡ ይህን አገልግሎት ለመደገፍ (Tesfahun Hatia Daka, Commercial Bank of Ethiopia, Andinet Branch; A/C 1000036318949; Swift Code: CBETETAA) መላክ ትችላላችሁ፡፡ ለዘሪ ዘርን የሚሰጥ ጌታ ዘራችሁን ይባርክልኝ!)

No comments:

Post a Comment