ዲቮሽን
ቁ.162/07፣
ሐሙስ፥
የካቲት
12/07 ዓ.ም.
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል!
እንግዲህ
ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሐ ግቡ፣ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፣ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል (የሐዋ 3፡19)።
መንፈሳዊ
ሕይወት ዕለት ተዕለት እየታደሰ መሄድ ይገባዋል፡፡ ይህ ተሐድሶ የሚመጣው ደግሞ፣ ንስሐ በመግባትና ከመንገዳችን በመመለስ ነው፡፡
ንስሐ ኃጢአትን የሚደመስስ መንፈሳዊ ኃይል ነው፡፡ የመታደስ ዘመን የሚመጣው ኃጢአታችንን ትተን፣ ከገዛ መንገዳችንም በንስሐ የተመለስን
እንደሆነ ነው፡፡
ወዳጄ
ሆይ፣ የመታደስ ዘመን እንዲመጣልዎ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ኃጢአትን ይተዉ፣ ከገዛ መንገድዎም ይመለሱ! በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን
ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነውና(1 ዮ 1፡9) በኃጢአታችን እንናዘዝ፣ ከመንገዳችንም እንመለስ። ይህ
ሲሆን ነው፣ የመታደስ ዘመን የሚመጣልን፡፡
የመታደስ
ዘመን ይሁንልዎ!
No comments:
Post a Comment